Thursday, October 4, 2018



                                                                            
አፄ ምኒሊክ

        በኢትዮጵያ ፖለቲካዊ ማህበራዊ ወታደራዊ እና ኢኮኖሚያዊ ሕይወት የራሳቸወን አሻራ አኑረው ካለፉ ጥቂት ከማይባሉ ነገስታት መካከል ዳግማዊ አፄ ምኒሊክ ንጉሰ ነገሥት ዘኢትዮጵያ እና እቴጌ ጣይቱ ፕጡል ብርሀን ዘኢትዮጵያ በሕይወት ዘመናቸው በግልም ሆነ በጋራ ለኢትዮጵያ እና ለሕዝቦቾ ባለውለታ ናቸው::
እቴጌ ምናልባትም በኢትዮጵያ ነገስታት ታሪክ ጠንካራ፣ቆራጥ፣ጀግና፣ብልህ እና አስተዋይ የሚባሉ ንግስት ነበሩ::

      ግማዊ አፄ ምኒሊክ የተወለዱት በነሐሴ 12 1836 ዓ.ም በእለተ ቅዳሜ ነበር በንጉስና በንጉሰ ነገስትነት ኢትዮጵያን የገዙበት የነገስታት ዘመን በድማር ፬፯ (47) ዓመት ከ  ፫ (3)ወር ነው  
   
      ምኒሊክ የ፲(10) ዓመት ልጅ ሳሉበ ፩፰፬፮ (1846) አፄ ቴዎድሮስ እና  ምኒሊክ አባት ሐይለ መለኮት መካከል ጦርነት ተካሄዶ አፄ ቴዎድሮስ ድል ስለነሱ አፄ ምኒሊክ እስረኛ ሆነው ወደ መቅደላ ተወሰደው ለ ፲ (10) ዓመት አፄ ቴዎድሮስ እስርቤት ከነበረው ከመቅደላ ቆዩ ከዛም አምልጠው በ ነሐሴ ፪፬(24) ፩፰፭፯(1857)ዓ.ም አንኮበር ላይ ባባታቸው በንጉሥ ሐይለ መለኮት ዙፋን ነገሡ ከዛን ጊዜ ጀምሮ አፄ ዮሐንስ ወደ ሸዋ እስከመጡ ድረስ ንጉሰ ነግስት ተብለው በሸዋ ለ፩፩ (11)ዓመት ከ ፮ (6) ወር ነገሡ

ማህተባቸውም
ሞዓ አንበሳ ዘመነገደ ይሁዳ ምኒሊክ ንጉሰ ነገሥት የሚል ነበር
     
       ንጉሰ ነገስት ዮሐንስ ከትግሬ ወደ ሸዋ ዘምተው ሳሉ በየካቲት ወር ፩፰፸(1870)ዓ.ም ገደማ በተደረገው ስምምነት ዳግማዊ ምኒሊክ የአፄ ዮሐንስ ንጉሰ ነገሥትነት ተቀብለው ዳግማዊ ምኒሊክ ንጉሰ ሸዋ ተብለው ፲(10) ዓመት ኖሩ በዚህ ጊዜ ማህተባቸውም ሞዓ አንበሳ ዘእም ነገደ ይሁዳ ምኒሊክ ንጉሰ ሸዋ ሆነ
ንጉሰ ነገስት ዮሐንስ

ንጉሰ ነገስት ዮሐንስ መተማ ላይ ከሞቱ በዋላ ዳግማዊ ምኒሊክ በመጋቢት ወር ፩፰፰፩(1881)ዓ.ም የኢትዮጵያ ንጉሰ ነገሥትነትን ተቀናጁ በንጉሰ ነገሥትነትም ለ ፪፬(24)ዓመት ከ ፱(9) ወር ነው



                                                   ግማዊ አፄ ምኒሊክ ንጉሰ ነገሥት ዘኢትዮጵያ
 እቴጌ ጣይቱ ፕጡል ብርሀን ዘኢትዮጵያ
 እቴጌ ጣይቱ ፕጡል ብርሀን ዘኢትዮጵያ


No comments:

Post a Comment